Telegram Group Search
የእኔ ታሪክ (ምዕራፍ -2)

ክፍል -4



እኔ ስኬትን አይቻለሁ፣ ውድቀትን አይቻለሁ፣ ፍቅር አይቻለሁ፣ እጣፈንታን አይቻለሁ፣ ሕመምን አይቻለሁ፣ መርሳትን አይቻለሁ፣ ጥንካሬን፣ ድክመትን፣ ተስፋ ማጣትን፣ ጥሎ መሸሽን፣ ስብራትን፣ ቁስለትን፣ መራር ሀዘንን......ብቻ ብዙ ነገር አይቻለሁ።ግን አለሁ(እንባውን ጠራረገ)........የሰው ልጅ ፅኑ ፍጥረት ነው። ሁሉን እንዲችል ተደርጎ ተፈጥሯልና።ታዲያ እንዴት ወደ ትውስታህ ተመለስክ......(እሷም እንባዋን ጠራረገች።


አብጄ በነበረ ሰዓት አንዲት ሴት አገኘችኝ። ያኔ እኔ የምለውን ነገር አላስታውስም ነበር እሷ ግን ስናገራቸው በነበረ ሰዓት ውስጧ ይነካ እንደነበር፣ እቤት ገብታም ስለ እኔ ከልቧ  ታለቅስ እና ትፀልይ እንደነበር ነገረችኝ። እማዬ? አለች ፊቷ ብርሃን እየሞላው ቀና ብላ እየተመለከተችው። አወ እናትሽ አላት ፈገግ ብሎ።



እናትሽ በህመሜ ውስጥ አፈቀረችኝ። ሰላም በማንነቴ ሳይሆን ባሉኝ ነገሮች ነበር የወደደችኝ አንድ ስህተት ስታገኝ ጥላኝ ጠፋች፣ ራቢያም በመላመድ ነበር ያፈቀረችኝ አድርግ ያለችኝን ባለማድረጌ ከእኔ ሸሸች አየሽ ራቢያ ከፍቅር በላይ መዋረድ አስፈራት፣ ሰላምም ከፍቅር በላይ ስሟ አሳሰባት ልጅ ያለው ሰው አገባች መባልን ተፀየፈች።


እናትሽ ግን እብድ ያውም ራሱን የማያውቅ የሚጠጣ እና የሚያጨስ ሰው አፈቀረች። ሰው መሆኔን ብቻ አየች ስለውጫዊ ማንነቴ ግድ ሳይሰጣት ውስጤን ብቻ ተመለከተች።ስሟ አላሳሰባትም፣ መዋረዷ ፣ መጠላቷ፣ መገለሏም አልታያትም ውስጧን ብቻ ተከተለች። ስለ እኔ ብዙ ተሰቃየች፣ ተጠላች፣ ተዋረደች ግን ተስፋ አልቆረጠችም ብዙ ለፍታ አዳነችኝ ። ከሞት ወደ ህይወት እንገና መለሰችኝ።ተሳካላት ያንን የወደቀውን ሕዝቅኤል እንደገና ሰው አደረገችው። ስለሷ ሲናገር ቃላት ያጥረዋል ከንግግሩ እንባ ይቀድመዋል ዛሬም የሆነው እንደዛ ነው። በብዙ አለቀሰ እሷም እንባዋን እያፈሰሰች አታልቅስ አባ አለችው ተነስታ ጉያው ስር እየተሸሸገች።
ይቀጥላል.........
@nibab_lehiwot
አጭር ታሪክ

ባጣ ቆየኝ???


እወደዋለሁ ብየ አስባለሁ......ግን ይሰለቸኛል.....ወሬው ያናድደኛል፣ ግን ደግሞ ደስ ይለኛል፣ እሱም ይወደኛል.... ግን እኔ የተሻለ ሰው ካገኘሁ እንደምተወው ይሰማኛል። ለዚህም ያስፈራኛል አንዳንዴም እርሱን መውደዴን እጠራጠራለሁ( ግን የእውነት ወድጄው ነው?) ራሴን መጥፎ ነኝ እንዴ ብየ ብዙ ጊዜ ጠይቄያለሁ? ለራሴ የምሰጠው መልስ ግን አንዳንዴ አይ አንዳንዴ ደግሞ አወ ነው። ግን የሰው ልጅ በተፈጥሮው ራስወዳድ ነው እኔም ራሴን ብወድ አጃኢብ ሊያስብል የሚችል ነገር አይደለም ሆ..... ሁሉም ሰው እያስመሰለ እንጅ ራሱን ይወዳል.... ታዲያ እኔ ከእሱ የተሻለ ሰው መመኘቴ ምኑ ላይ ነው ስህተቱ ኧ? የተሻለ ስራ ያለው፣ የተሻለ እውቀት ያለው፣ የተሻለ መልክ ያለውየተሻለ የሚወደኝየተሻለ የሚንከባከበኝ......እህ ምኑ ላይ ነው ስህተቱ አንዳንዴ ሾጥ አድርጎኝ ማስቲካየን ጧ ጧ ፣ ጫማየን ቋ ቋ እያደረግኩ ሔጄ ልክ አቀርቅሮ መፅሀፍ እያነበበ ያለበት ቦታ ሔጄ ስማ ካንተ የተሻለ ሰው ካገኘሁ ልተውህ እችላለሁ ብየ ብነግረውስ.....ከዛ እሱ ደሞ እባክሽ አትተይኝ ትወጅኛለሽኮ የተሻልኩ እሆናለሁ አንቺ እንደምትፈልጊው ሲለኝ ኪኪ... ህህህ ወይ ደሞ ለምን የተሻለ እስክታገኝ ትጠብቂያለሽ በይ አሁን ከፊቴ ጥፊ "ባጣቆየኝ" አረግሽኝ አ ብሎ በጥፊ ቢያላጋኝስ..... መቼም ዝም አልለውም በጠርሙስ አናቱን ብየ ነው ምገላግለው.........እግዚኦ በሰላም እየኖርን ካለሁት ፍቅረኛየ ጋር ይሔንን ሀሳብ ማሰብ ምን ይሉታል? ወይ ቅሌት አሉ ..... ግን ባጣ ቆየኝ ማለት? ምን አገናኘው አሁን እሱ የእኔን ጭንቅላት ማንበብ ቢችልስ? ከዛ ፍቅረኛየ ሳይሆን ባጣቆየኘ እንደሆነ ቢያውቅስ ህእ ......... ያስፈራል ከዛ ጠላሁሽ ቢለኝስ? ወይ ደግሞ እኔ ራሴ ከአንቺ ሌላ በሁሉ ነገር የተሻለች ፍቅረኛ አለኝ ስለዚህ አንችም ባጣቆይኘ ነሽ ቢለኝስ ወይኔ ጉዴ ምን ላደርግ ነው?.........ግን እሱም የተሻለ እስኪያገኝ ቢሆንስ ከእኔ ጋ የሆነው በምን አውቃለሁ ጭንቅላቱን አላነብ.......... የምር ባጣቆይኙ ብሆንስ😳


በሉ በሉ "ስራ ከመፍታት ልጄን ላፋታት አለች" አሉ ማን ነበር ስሟ አላውቅም ማንም ትሁን ብላለች ተብሏል እኔም ስራ ፈትቼ ፍቅረኛየን ከምፈታ በሰላም ወደ ስራየ ልስራሆ ሰው በራሱ ጊዜ ሰላሙን ያጣል ? ሳስበው ግን የአለም 70% ፍቺ ስራ ከመፍታት የሚመጣ ይመስለኛል ያው የኔው ጥናት ነው።

ረድኤት ተነሽ ወደ ስራ........ቅድሚያ ግን ለባጣቆየኘ ማነው ለፍቅረኛዬ ልደውልለት ደህና ዋሉ።
😁

@nibab_lehiwot


@nibab_lehiwot
🕊ሀሙስ🕊
ክፍል-1

ከእለታት በአንድ ሀሙስ እንዲህ ሆነ። ያው የለመድኩትን የበቀቀን ኑሮ እየኖርኩ እነሱን እያደነቅኩ የእነሱን ህይወት እየናፈቅኩ በእነሱ ስብከት ልቤን ቅልጥ እያደረግኩ "i am a single lady " የሚል ዘፈን በኤርፎን ከፍቼ እንደ እብድ ብቻየን እየጮህኩ በጠዋት ተነስቸ  ወደ የት እንደምሄድ ሳላውቅ ዝም ብየ ወደ ፊት እየተጓዝኩ ድንገት አንድ ድምፅ ከኋላየ ሲጠራኝ ተሰማኝ ዘወር አልኩ።አንድ  ሽማግሌ አባት ነበሩ። በእጃቸው ብቻ ወደ እሳቸው እንድመጣ ጠሩኝ።ለምን እንደሆነ አላቅም ሳላንገራግር ቀጥ ብየ ሄድኩ።በተለመደ ሰላምታ ደህና ዋልሽ አሉኝ።እኔም ይመስገን .......መለስኩላቸው። ማንነትሽ ምንድነው? ብለው ጠየቁኝ....... እህ ግራ ገባኝ ምን ለማለት ፈልገው ነው?
bee
🕊️ ሀሙስ🕊️
ክፍል -2

ሰው እንዴት ከመሬት ተነስቶ እንደዚህ አይነት ጥያቄ ይጠየቃል አልኩ ለራሴ......ከዛም እ ማለት አልገባኝም ምን ለማለት ፈልገው ነው አልኳቸው። ኤርፎኔን ከ ጆሮየ እያወለቅኩ። እሺ ዜግነትሽ ምንድነው ?አሉኝ
እ እንደዛ ነው እንዴ ኢትዮጵያዊ ነኛ አልኩ ቀለል አድርጌ።
እርግጠኛ ነሽ ? አሉኝ በአትኩሮት እየተመለከቱኝ እንዴ ይሄ ሰውየ ምን አስቦ ነው ብየ በድጋሜ በውስጤ አወራሁ።
አዎ ምነው ?አልኳቸው። እሽ በይ እንግዲያውስ ምንሽ ኢትዮጵያዊ እንደሆነ ንገሪኝ? እስኪ ራስሽን ተመልከች ...አለባበስሽ፣አናኗኗርሽ፣አስተሳሰብሽ፣አመጋገብሽ፣ ምኞትሽ ሳይቀር ፈረንጅ መሆን አይደለምን? አሉኝ በጣም ደነገጥኩ  እንዴት አወቁ ?ብየ ጠየኩ
እሱን ተይውና የጠየኩሽን ብቻ መልሽ.....አሉኝ ረጋ ባለ ድምፅ.......ኦኦ ጠንቋይ በዝቷል ሲሉ የሰማሁት ትዝ ብሎኝ (ጠንቋይ ናቸው እንዴ አልኩ በውስጤ ) ፍጥጥ ብለው ሲያዩኝ ያሰብኩትን ያወቁብኝ መስሎኝ ሽምቅቅ አልኩ።

bee
🕊️ሀሙስ🕊️
ክፍል-3

አዎ ልክ ነወት ግንኮ እነሱን መሆን መመኘቴ ምንም ክፋት የለውም።እውቀት አላቸው፣ ጥበብ አላቸው ፣ብዙ ነገር መስራት ይችላሉ ፣ደግሞም በጣም ትጉህ ናቸው።ታዲያ ለምን እነሱን መሆን አልሻም አልኩ በሙሉ የራስ መተማመን።

ፊታቸውን ፈገግ አደረጉት ከዛም ወዳያው ኮስተር አሉ።ጥሩ ነው ስለ እነሱ በደምብ ታውቂያለሽ እውቀታቸው የስርቆት ፣ ጥበባቸው የሰይጣን ፣ስራቸው በተንኮል ፣ትጋታቸው እኛን ስለማጥፋት....... መሆኑንስ ታውቂያለሽ ?
እኚህ ሰውየ እብድ ይሆኑ እንዴ ? ዘንድሮኮ ኑሮ ያላሳበደው የለም በማን መፍረድ ይቻላል? እያልኩ ከራሴ ጋ በውስጤ ሳወራ ለሳቸው መመለሴን ዘንግቸው ኖሮ........በድጋሚ እሽ ይሄን ተይው ኢትዮጵያዊ መሆንንስ አትመኚም ? አሉኝ በመገረም እየተመለከቱኝ።.......እንዴ ኢትዮጵያዊ ሆኜ ለምን ኢትዮጵያዊነትን እመኛለሁ።አልኩ ግራ በገባው አነጋገር።
ደግ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብለሻል። በይ እንግዲህ ስለ ኢትዮጵያውያን ስራ ንገሪኝ ?ምን እንዳደረጉ ተርኪልኝ።መቸም የራሱን ሀገር ታሪክ የማያውቅ ዜጋ የለም።ስለዚህ በደምብ አስረጂኝ.........
ፈጣሪየ ሆይ በጣም ደነገጥኩ ።እኔ ሲጀመር ያለ ማጋነን ስለ ኢትዮጵያ ምንም አላውቅም።
የማውቀው እንደምጠላት ብቻ ነው
bee
🕊️ሀሙስ 🕊️
ክፍል-4

ምን ብየ ልመልስ ምላሴ ተሳሰረ።ልክ ናቸውኮ ምንም አላውቅም።አንገቴን ደፍቼ ዝም አልኩ.......
ይሄኔ ስለነ አልበርት፣ ስለነ ቶማስ ኤዲሰን ፣ ስለነ ጀምስ ብሩስ ፣ ስለነ አብርሀም ሊንከን ፣ ስለነ ክርስቶፈር ኮሎምበስ .............
ብጠይቅሽ ኖሮ ሁሉንም በትክክል ትመልሽ ነበር አደለም? አሁን ንግግራቸው ወደ ቁጣ እያመራ መጣ።የኔ ልብም  እንዲሁ በፀፀት እየደማ መጣ።በእፍረት አንገቴን በ አዎንታ ነቀነቅኩ።


በይ እንጅ ስለነ ቅዱስ ያሬድ ንገሪኝ ፣በይ ስለ ካህኑ ዮቶር አስረጂኝ ፣ በያ ስለ ሊቁ ተዋነይ ተርኪልኝ ፣ቶሎ በይ ስለ ቅዱስ ላሊበላ ንገሪኝ ፣በይ ስለ ህንደኬ ፣ስለ ንጉስ ኢትኤል ፣ስለ ኢትዮጵያዊው ቢላል  ፣ስለ ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ፣ ስለ ሔኖክ፣ስለ ባልቻ አብዲሳጋ ፣ስለ ራስ አሉላ...ንገሪኝ..ስለ ንግስተ ሳባ.................በጣም ብዙ የማላውቃቸውን ስሞች ጠሩ።ምንም አላውቅም አልኩኝ።


አየሽ ታዲያ እንዴት ኢትዮጵያዊ ልትባይ ትችያለሽ ኧ?
ንገሪኝ እስኪ እነዚህ ሰወች ድንጋይ ፈልፍለው አለት ጠርበው ህንፃን አነፁ ፣ኢትዮጵን በስልጣኔ አሳደጉ ፣ዜማ ቅኔ ማህሌትን ለአለም አስተማሩ ፣ብራና ፍቀው ቀለም በጥብጠው ፣ የፅሁፍን ጥበብ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአለም አስተማሩ፣ የአመራርን ስርዐት በምድር አሳወቁ ፣ ለሀገራቸው ሲሉ መስዕዋት ሆኑ ፣ ለእሷ ሲሉ ህይወታቸውን ያለምንንም ስስት ገበሩ፣ ኧረ ስንቱን ልበል ጥበባቸው ስራቸው ተነግሮ አያልቅም።እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው።ተባሉ አንቺም ታሪክሽን እንኳ ሳታውቂ ኢትዮጵያዊ ነኝ አልሽ? መልሽልኝ።.......


bee
🕊️ሀሙስ 🕊️
ክፍል-5

አውቃለሁ........     ሊያምሽ ይችላል አወ እንዲያምሽ ነው ምፈልገው ለመዳን የግድ በደምብ መታመም አለብሽ።......ንግግሩ መላ ሰውነቴን ይሰረስረው ጀመር።ምንም ሳላስብበት እንባ ከአይኖቸ ለመውጣት ያቆጠቁጥ ጀመር።ልቤን የሆነ ነገር የወጋኝ ያህል አመመኝ።
ምንም ቃል ለመናገር አንደበቴ እምቢ አለኝ። አ.....አዎ  ልክ ነወት እኔስ ኢትዮጵያዊ የሚለው ክብር አይገባኝም ብየ በሁለት እጆቸ አይኖቸን ጠራረግኩ።እንባየ ግን አልቆመም።


አሁን ማልቀስ መፍትሔ አይሆንም ከተኛሽበት ንቂ።አሁን በድጋሚ ልጠይቅሽ ኢትዮጵያዊ መሆን አትመኝም ?
......... በደምብ ነው ምፈልገው  አልኩዋቸው ከልብ በሆነ ስሜት....
እ አባባ አንድ ጥያቄ መጠየቅ እችላለሁ አልኩ እንዳቀረቀርኩ።
አዎ ጠይቂኝ ከመጠየቅ ነው ጥበብ ሚገኘው እግዜርስ ጠይቁ ይሰጣችሁማል አይደል ያለው .............ዝም ብለሽ የነገሩሽን ከማመን ጠይቂ መጠየቅ ጠቢብ ያደርጋል።
እሽ ግን ለምን ይሄ ሁሉ ታሪክ እያለን ፣ሁሉም ነገር የኛ ሆኖ እያለ ፣ጥበብ ሁሉ ተሰጥቶን .......
ለምን ተሰወራችሁብን ፣ለምን ግልፁን አትነግሩንም ፣ ለምን ዝምታን መረጣችሁ አልኩት........

bee
🕊️ሀሙስ 🕊️
ክፍል-6

ፈገግ አሉና ""የተሰወርነው እኛ ሳንሆን የተሰወራችሁት እናንተ ናችሁ"" አሉኝ።
ኧ.........ምን ማለት ነው ይሄ? ድጋሚ ጠየቅኩ
ይሄን ማወቅ ያለብሽ አንች ነሽ እንግዲህ ኢትዮጵያዊ ለመሆን እንደሻትሽ ነግረሽኛል።አሁን ነቅተሻል ስለዚህ መርምሪ ፣ ለማወቅ ቆፍሪ ፣በደምብ ጣሪ......የተቻለሽን ሁሉ አድርጊ ያኔ ሁሉንም በደምብ ታውቂያለሽ አለኝ።
እኔም አሁንማ ምን ዋጋ አለው ሁሉም አልፏል ወደፊት ልቀጥል እንጂ አልኩኝ።እሳቸውም የመስቀል ቅርፅ ያለውን መቋሚያ ተደግፈው ቆሙ ።አልረፈደም ደግሞ  ''ከሚቀር ሰው አርፍዶ የመጣ ተስፋ አለው''።' ኢትዮጵያ የምታድገው ወደ ፊት በመራመድ ሳይሆን ወደኋላ በመጓዝ ነው።" ብለውኝ መንገዳቸውን ቀጠሉ።እኔም እንደቆምኩ ሀሳቤን ቀጠልኩ።


ልክ ነበሩ አዎ አንቀላፍተናል።ዝም ብለን የሚሰጡንን እየዋጥን ደንዝዘናል።ከማንም በላይ ታላቅ ሀገር ይዘን ፤ታላቅ ታሪክ ተሰጥቶን በእጅ የያዙት ወርቅ እንደመዳብ ይቆጠራል እንዲሉ አበው እኛም የሰውን ስንመኝ በተቆፈረልን ጥልቅ ጉድጓድ ዘው ብለን ገባን።እኛ ማለት ትተን እኔነት መረጥን።ይሄም ውጤቱ  በዘረኝነት በሽታ ተለክፈን ይኸው ስንት አመት ተባላን።እርስ በርሳችን መጠባበቅ ሲገባን መገዳደልን መረጥን ።በዚህ የተጠቀምን መስሎን ሀገራችን ጎዳን እንደገና ዝቅ አልን።


አሁን ከገባንበት ጉድጓድ የመውጫ ጊዜያችን ነው።የነፃነታችን ሰዓቱ ደርሷል።ምንም እንኳ ጉድጓዱ ጥልቅ ቢሆንም እጅ ለእጅ ተያይዘን መውጣት አያቅተንም።ምክንያቱም እኛ ኢትዮጵያውያን ነን ።ወደፊት ቀዳሚ ታላቅ ህዝቦች።ይሄንን ከራሴ ጋ ሳወራ ለካ ሰዓቱ ሄዷል። እሳቸውም ከእኔ ተሰውረዋል። እኔም ወደፊት መሄዴን ትቸ መንገዴን ወደኋላ ቀጠልኩ።
ይህቺን ቀን ግን ወደድኳት ማንነቴን ያወቅኩባት እለት ።መቸም ላልረሳት ለራሴ ቃል ገባሁ። 🕊️"ሀሙስ የቀን ቅዱስ"🕊️

ተፈፀመ።

bee
የእኔ ታሪክ (ምዕራፍ -2)

ክፍል -5

አባዬ አለችው እቅፉ ውስጥ እንዳለች....አቤት አላት ጎንበስ ብሎ እየተመለከታት።
እሷ:- እ.... ወንድሜን ግን ለምን አንፈልገውም?
እሱ:- አይሆንም ልጄ ለ እኔ አንቺ ሁሉ ነገሬ ነሽ ሌላ ማንም ሰው አያስፈልገኝም በአንቺ ውስጥ ብዙ ሰዉ አያለሁ ለእኔ አንድ ብቻ ሳትሆኝ ብዙ ነሽ።
እሷ:- አባ ለ እኔ የምታሳየኝ ፍቅር አንድም ጎድሎብኝ አያውቅም፣ እባክህ ወንድሜ እንዳንተ አይነት አባቱን ሳያውቅ እንዲሞት አታድርግ፣ እኔም ታላቅ ወንድም እያለኝ እሱን ሳላገኝ እንድቀር አትፍረድብኝ። ደሞ አውቃለሁ ሁሌም እሱን ባለማግኘትህ እና ባለማየትህ ውስጥህ ይሰቃያል። ምንም ያክል ልትደብቀው ብትሞክርም ይታየኛል።

ሕዝቅኤል በሀዘን ብዛት የጎደጎዱ አይኖቹን አሻግሮ ማዶ ማዶ እያየ እንዲህ ያስባል። እውነትም ልጄ ውስጤን ታነባለች፣ የአብራክን ክፋይ በአይን ሳያዩ ለ እነዚህ ሁሉ አመታት መቆየት ሕመሙን በቃል መግለፅ ባይቻልም ግን የደረሰበት ያውቀዋል።



አባ እኔ ራሴ ሄጀ ወንድሜን እፈልገዋለሁ ሔራ ከተቀመጠችበት ፈንጠር ብላ ተነሳች። ሕዝቅኤል አጮምጩመው ሊጠፉ ደርሰው የነበሩ አይኖቹ ከመቅፅበት ተጎለጎሉ። ሔራ ይሄ የቂል ሀሳብ ነው እንደውም እንዳልነገርኩሽ እርሽው።
አይሆንም አባ እሄዳለሁ! አለች ሔራ ኩስትር እያለች....ልጄ እስካሁን ያጣኋቸው ሰወች ይበቁኛል። አንድ አንቺ ብትኖሪኝ አንቺንም አጥቼ በስቃይ እንድሞት አታድርጊኝ። እንደ አባት አንቺን የማዘዝ መብት አለኝ እንደ ልጅ ደግሞ የመታዘዝ ግዴታ አለብሽ ቪቪያን!!!
ወደዛች የተረገመች ሀገር እኔ ሳልሞት አትንቀሳቀሽም ከቀበርሽኝ በኋላ መሔድ ትችያለሽ።

አባ...... ቪቪያን እዝን አለች። ምንም እንድትይኝ አልፈልግም ሔራ ወደ ውስጥ ግቢ....... ሔራ አንገቷን አቀርቅራ ወደ ውስጥ ገባች።


ሕዝቅኤል ግን ከእንደገና የልጁ ነገር ያሳስበው ጀመር።

ይቀጥላል.......


@nibab_lehiwot
ከታዘብኩት.......


እያንዳንዳችን ለምን ብለን ብዙ ጠይቀን መልስ ያጣንላቸው ጥያቄወች በውስጣችን አሉ። ማጥፋት ፈልገን የማይጠፉ፣ ማመን ፈልገን የሚያጠራጥሩን፣ መርሳት ፈልገን የማይረሱን፣ ብቻ ብዙ ብዙ ነገር ውስጣችን አለ። (የዛሬ ጥያቄዬ ለምን ብቻውን የሚያወራ ሰው እብድ እየተባለ ይጠራል?)


አንዱ ነውኮ...... ዛሬ ብቻውን እያወራ እየሔደ ይሄ ሰውዬ እብድ ነው ብሎ ጭንቅላቴ ደመደመ። በመጀመሪያ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከንፈሬን መጠጥ አድርጌ ኑሮ ያሳበደው ምስጊን ሕዝብ አልኩ (በውስጤ) ይሔንን ስል ግን አንዱ የአእምሮየ ክፍል(ምን እንደሚባል እኔ እንጃ) ድንገት ከተኛበት በቀዝቃዛ ውሃ እንደተዘፈቀ ሰው ብንን ብሎ ነቃ........

እሱ:- ለምን እብድ መሰለሽ?

እኔ:-ብቻውን እያወራ ነዋ.....

እሱ:- ብቻ ማውራት እንደ እብድ እንደሚያስቆጥር እንዴት አወቅሽ.......

እሱ:- ቀላል ጥያቄ ከልጅነቴ ጀምሮ እያየሁት እና እየተነገረኝ ያደግኩት ብቻውን የሚያወራ ሰው ጤነኛ እንዳልሆነ ነው።


እሱ:-እና ስለተነገረሽ ብቻ አምነሽ ተቀበልሽ አትጠራጠሪም?

እኔ:- ለምን እጠራጠራለሁ?

እሱ:- ለምን አትጠራጠሪም?..........


(በጣም ብዙ ብዙ... የለምን? ክርክር)

እሱ:- ማስረጃ አቅርቢ.....

እኔ:- አንተ ማስረጃ አቅርብ.....

እሱ:- እብድ ነሽ እንዴ?

እኔ :- አይደለሁም

እሱ:- ነሽ

እኔ :- ለምን እንደዛ አልክ?

እሱ:- ብቻሽን እያወራሽ ነዋ

እኔ:- እንዴ መቼ?

እሱ :- አሁን !!!

እኔ:- ከአንተ ጋ አይደል እንዴ እያወራሁ ያለሁት

እሱ:- ማን ነኝ እኔ እስኪ ዞር ዞር በይ እኔ የለሁምኮ

አንዴ ወደ ግራ አንዴ ወደ ቀኝ ዞር ዞር አልኩ ማንም የለም። አማተብኩ ከማን ጋ ነበር እያወራሁ የነበረው?

እሱ:- አየሽ እብድ ነሽ ያው ማስረጃ ብቻሽን እያወራሽ ነው........

እኔ:- ዝም በል......ሳላስበው ዛፍ ላይ የነበሩት ወፎች በድንጋጤ እስኪበሩ ድረስ ጮህኩ።
በረጅሙ ተነፈስኩ እና አካባቢየን ቃኘት አደረግኩት። ለራሴ የተሰማኝ ከሆነ ቦታ ቆይቼ አሁን ወዳለሁበት ቦታ እንደተመለስኩ ነው።


ወይኔ ጉዴ ሰው ሁሉ ወደ እኔ እያፈጠጠ ነው።




አበድኩ እንዴ?🤔


@nibab_lehiwot
@nibab_lehiwot
@nibab_lehiwot
አንዳንዴ የተሳሳተ መንገድ የምንመርጠው ምናልባት ከጀርባ ሆነው በሚጎትቱን ሰወች ነው። ከገባንበት ለመውጣት ወደ እነርሱ ስንዞር ደግሞ ከአጠገባችን ተሰውረዋል።

@nibab_lehiwot
በመንገዴ ላይ...........

አንድ ቀን ነው አንዲት መልኳ እንኳን እዚህ ግባ የማይባል አይነት ሴት ነች። ድንገት እያለፍኩ ከኋላ ጠራችኝ።
ያው እንደተለመደው ስልኬን ከሚጠይቁኝ ብዙ ሴቶች አንዷ ነች ብየ ኩራት በተሞላበት መንፈስ ቀስ ብየ ዘወር አልኩኝ ሳላጋንን በጣም ብዙ ሴቶች የሚወዱት አይነት መልክ፣ ቁመና፣ ስራ እንዲሁም ስብዕና ያለኝ ወጣት ነኝ። ልጅቷ በጣም የተቻኮለች ትመስል ነበር ሰዓት ንገረኝ እባክህ ? ያው እኔን ለማውራት ሰበብ እንደሆነ ገባኝ እና ኮራ ብየ የእጅ ሰዓቴን ተመለከትኩት። 3:00 አልኳት አይኗ ፈጠጠ እዛው በቆምኩበት ጥላኝ ሮጠች። ምን ሆነሽ ነው ብየ እንድከተላት ነው መቼስ ይሄ ሁሉ አይ ሴቶች በቃ መንገድ አያጡም አይደል ብየ በቆምኩበት ፈገግ እንዳልኩ እያየሁ በአይኔ ሸኘኋት።


ሮጠች ሮጠች ልቧ እስኪጠፋ ሮጠች...... አልተከተልኳትም ግን ድካሟ ተሰማኝ የት ነው ምትሮጠው?
ለምን እንደዚህ ደነገጠች? እውነትም እኔን ለመተዋወቅ ብላ ባይሆነስ....... አይ ምን አገባኝ ..... የቆመች መኪናየ ውስጥ ገብቼ ወደስራየ መሄድ ጀመርኩ።


ድንገት ያቺ እንደ ሚዳቋ ስትፈጥን የነበረች ልጅ ተቀምጣ አገኘኋት።
እኔን ስታይ ፈጠን ብላ ተነሳችና እጇን እያውለበለበች ፈገግ አለች። መኪናየን አቆምኩ እና አቤት አልኳት እባክህ ሸኘኝ.... .. አረጋገጥኩ በቃ ከእኔ ጋ ለመግባባት ስቃይዋን እያየች ነው። ግን ለወጉ ወደየት ነሽ? አልኳት ወደ ሳሪስ አለች የሚገርመው እኔም መንገዴ ወደዛ ነበር። ከእኔ ጋ ለመግባባት ሳይሆን እኔን "ለመብላት" ነው ሚለት በእነሱ ቋንቋ በማሰቧ ከልቤ አዘንኩላት እና አይ ስራ ረፍዶብኛል ይቅርታ ሌላ ሰው ጠይቂ ብያት መስኮቱን ዘጋሁት። ከዘጋሁት በኋላ የሆነ ነገር እያለችኝ ነበር ግን አልሰማኋትም ወደፊት ነዳሁት።(እንደዚህ አይነት ሴቶች ያናድዱኛል "ጎልድ ዲገር" እንደሚባሉት ያሉ መኪና እና ቤት ያላቸውን ሞኝ ወንዶች የሚያሳድዱ እሷም ከእነሱ መሀል ነች።)

በዋናነት ግን የህክምና ባለሙያ በመሆኔ እሷ በምታወራቸው ወሬወች ራሴን አናድጄ መሄድ አልፈለግኩም ታካሚወቼ ላይ ምንም ተፅእኖ እንዲደርስ አልፈልግም ። ለዛም ነው ከአላስፈላጊ ሰወች እና ወሬወች ራሴን የማርቀው በእጄ የያዝኩት የተከበረውን የሰው ልጅ ህይወት ነውና።


ስራ ገባሁ
አንድ ታካሚ በፍጥነት ኦፕሬሽን መሆን ነበረበት ነገር ግን የሚፈርምለት ቤተሰብ ቶሎ መድረስ አልቻሉም ። ሆስፒታሉ ውስጥ ትልቅ ክርክር ተነሳ ግማሾቻችን ቤተሰቦቹ እስኪመጡ አንጠብቅ አልን። ሆስፒሉ ደግሞ ሃላፊነቱን አልወስድም አለ። በዚህ ተናድጄ ቆየሁ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ሰወቹ ደርሰው ፈረሙ እና ወደ ቀዶ ጥገናው ክፍል ገባን። የአቅማችንን ሁሉ አደረግን ግን ልናተርፈው አልቻልንም።በህይወቴ እንደዚህ የተናደድኩበት እና ያዘንኩት ቀን ትዝ አይለኝም። ተስፋ በቆረጠ አረማመድ እየተራመድኩ ወጣሁ ቅድም ያገኘኋት ልጅ አንገቷን ደፍታ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች አየኋት ።


አይኔን ማመን አልቻልኩም ምን ትሰራለች እዚህ????? አባቷ ናቸው ያረፉት ዶክተር አለች አንዷ ነርስ ከኋላዬ........



ትንፋሽ አጠረኝ በእኔ ምክኒያት ሰው ሞተ? ለታካሚወቼ የምጨነቀው እኔ ራሴ ታካሚወቼን ገደልኳቸው።

ሁሌ ራሴን ትክክል አድርጌ ማሰቤ ትልቅ ስህተት ነበር። ካጋጠሙኝ በጣም ተደጋጋሚ ነገሮች አንፃር ቢሆንም ያደረግኩት ግን ልክ አልነበርኩም። አንዳንዴ ከአንዳንድ ውሳኔወቻችን እና ግምቶቻችን በፊት ቆም ብለን ማሰብ ያስፈልገናል።


ከተቀመጠችበት ሆና አንገቷን ቀና አድርጋ አየችኝ ምናልባት የአባቴ ገዳይ ፣ ጨካኝ፣ አውሬ እያለችኝ ይሆናል በውስጧ) እኔም እየተራመድኩ አንገቴን ሰበር አድርጌ አይቻት


እኔም መንገዴን እሷም ለቅሶዋን ቀጠልን......


ከዚያ ቀን በኋላ በህይወት ዘመኔ አይቻት አላውቅም። ግን አይኗ እስካሁንም ድረስ ይገርፈኛል


መስኮቱን ዘግቼው እያለ ምን ይሆን ያለችኝ ?


@nibab_lehiwot
ከ አርምሞ የተወሰደ።


እንድታነቡት ጋበዝኳችሁ
😊
ሕይወትን - በገፅ
የእኔ ታሪክ (ምዕራፍ -2) ክፍል -5 አባዬ አለችው እቅፉ ውስጥ እንዳለች....አቤት አላት ጎንበስ ብሎ እየተመለከታት። እሷ:- እ.... ወንድሜን ግን ለምን አንፈልገውም? እሱ:- አይሆንም ልጄ ለ እኔ አንቺ ሁሉ ነገሬ ነሽ ሌላ ማንም ሰው አያስፈልገኝም በአንቺ ውስጥ ብዙ ሰዉ አያለሁ ለእኔ አንድ ብቻ ሳትሆኝ ብዙ ነሽ። እሷ:- አባ ለ እኔ የምታሳየኝ ፍቅር አንድም ጎድሎብኝ አያውቅም፣ እባክህ…
የእኔ ታሪክ (ምዕራፍ -2 )


ክፍል 6

ቪቪያን ከ እናቷ ጋ እየተነጋገረች ነው። እማዬ እንዴት ልንገረው......... በጣም ጭንቅ እንዳላት ከፊቷ ያስታውቃል። ልጄ በጭራሽ ይሄንን ነገር ከአባትሽ እንድትደብቂ አልፈልግም ዛሬ ትንሽ መስሎ የተደበቀው ነገር ነው ለነገ ሌላ ትልቅ መዘዝ ይዞብን የሚመጣው። ችግርን ሳያድግ ነው ከስሩ መቁረጥ....... ግን አቋሙኮ ያስፈራል ቢከለክለኝስ? ምንም ይሁን ንገሪው ቪቫን እናቷ ተቆጣች። እሽ እማየ አሁን እነግረዋለሁ አለች አይኖቿን እያቁለጨለጨች( ቪቪያን ፀጉሯ በጣም ለስላሳ እና ረጅም ክብ ፊት እና ትልልቅ አይኖች ያሏት ውብ ሴት ነች)። ሕዝቅኤል እንደሚለው ፀጉሯ የራቢያን ፀጉር ያስታውሰዋል።
ከእናቷ ጋ ተለያይታ በረንዳ ወደተቀመጠው አባቷ በቀስታ ተራመደች።

አባዬ አንድ የምነግርህ ነገር ነበረ..... እና ንገሪኛ የኔ ትንሽ ርግብ በስስት ያያታል። ቪቪያን ለእሱ ልጁ ብቻ አይደለችም ሳቋ ሳያስደስታቸው የሞቱት እናቱ ንግግሯ አባቱን ፣ እልከኝነቷ ሳይጠግበው የተለየው ጓደኛውን፣አይኗ ያቺ ትንሽ የነበረችው እህቱን፣ ፀጉሯ ሳያገኝ ያጣው ፍቅሩን(ልጁን) ብቻ በቪቪያን ውስጥ ሕዝቅኤል ሙሉ ህይወቱን ያያል።እሷ ሁሉ ነገሩ ናት። ለሕዝቅኤል መኖር የ ቪቪያን መኖር ግዴታ ነው።



ግን አትቆጣኝማ አለች ፈገግ ብላ ጉንጩን እየሳመች። አንቺ አጭበርባሪ ምን አድርገሽ ነው አላት እድሜም ብቻ ሳይሆን ሀዘን ያጨማደደው ከንፈሩን በግድ ፈገግ እያደረገ። እሷም ሁልጊዜ እንደምታደርገው እግሩ ስር ተቀምጣ ራሷን ጭኑ ላይ አስደገፈች ህዝቅኤልም በተመሳሳይ ሁሌ እንደሚያደርገው ለስላሳ ፀጉሯን መዳሰስ ጀመረ። አባ አሁን አድጌያለሁ እና ፍቅረኛ ይዣለሁ በቃ እኔ ካንተ ምንም ልደብቅ አልችልም። ሕዝቅኤል ያልጠበቀው ነገር ስለነበር ደነገጠ እውነትም ልጄ አድጋለች። አለ በውስጡ ምነው አባ አትመልስልኝም እንዴ?..... እሱ ሲደነግጥ እሷም ተርበተበተች። ሕዝቅኤል ግን ያስደነገጠው ፍቅረኛ መያዟ አልነበረም ከዛ በኋላ ቤቱን ጥላ መውጣቷ እንጅ.......ቤት ውስጥ ከሌለች ምን እንደሚሆን ሲያስብ ጨነቀው።

ርግብ ሁሌ ከእኔ ጋ አትኖሪምኮ አንችም የራስሽን ሕይወት መኖር አለብሽ። ቪቪያን ደስ አላት። ባይሆን የልጄን ልብ ያሸነፈው ማን ነው?


ሁለተኛው ከባድ ጥያቄ ሆነ ለቪቪያን ። ምክኒያቱም ሕዝቅኤል በጭራሽ እንደማይቀበላት ታውቃለች። ግን የግድ መናገር ስለነበረባት እንደምንም ተርበትብታ ተናገረች። አ...አያን......


ምን...........ሕዝቅኤል ጮኸ።

ይቀጥላል ...........

@nibab_lehiwot
@nibab_lehiwot
@nibab_lehiwot
ጥበቃ.......

"እንዴት የሚያምር ቀን ነው"። በሚል ሀይለቃል ነበር ቀኔን የጀመርኩት። በጣም ደስ ብሎኝ ነበር በጠዋት የነቃሁት። ምክኒያቱም ለ 5 አመታት ሳልሰለች የጠበቅኩት ፍቅረኛዬ ይመጣል ። ለ አመታት ያሳለፍኳቸውን የጥበቃ ጊዚያቆች ሳስብ አንዳንዴ በፅናቴ እገረማለሁ። ከአሁን አሁን ይደውላል ጥበቃ፣ ከዛሬ ነገ ታገቢኛለሽ ብሎ ይጠይቀኛል ጥበቃ፣ ድንገት መጥቶ ሰርፕራይዝ ያደርገኛል ጥበቃ፣ ተኝቼ በህልሜ እስካየው ጥበቃ፣.................ብቻ ብዙ ብዙ ጥበቃ ለወትሮው እንደዚህ ትዕግስተኛ አልነበርኩም የያዘ ይዞኝ እንጅ........




ዛሬ ግን ይሄ ጥበቃየ ለመጨረሻ ጊዜ የሚያበቃበት ቀን ነው። በቃ እፎይ የምልበት ቀን። ለዛም ነው በጠዋት ተነስቼ ቆንጆ ሆኜ የመጨረሻ ጥበቃየን ለመጠበቅ እየተዘጋጀሁ ያለሁት ። የሚወደውን ቆንጆ ሀምራዊ ቀሚስ አድርጌ፣ ፀጉሬን በግራ በኩል ከፍዬ ቆንጆ አድርጌ አስይዤዋለሁ። ጫማዬ ጥቁር ትንሽ ተለቅ ያለ ሄል ያለው ቆንጆ ጫማ ነው። ቦርሳዬ ዋው እሱ ድሮ የላከልኝ በጣም ምወደው ጥቁር ነጫጭ ፈርጥ ያለው ነው። በጊዜው ውድ የሚባለውን ሽቶ በላዬ ላይ አርከፍክፌ መስታወት ፊት ቆምኩ። መልኬ እንደዛሬ ቆንጆ ሆኖ ታይቶኝ አያውቅም። ብቻ ወጣሁ..............



ቦታው ጋ ደርሼ ሲመጣ ምን እንደምለው ፣ ከዛ በኋላ የምናደርጋቸውን ነገሮች፣ የሚኖረንን ሕይወት እያሰብኩ በደስታ አለም ውስጥ ራሴን አሰመጥኩት። ጠበቅኩ.....ጠበቅኩ...... ጥበቃው ሊሰለቸኝ ሲጀምር..... ለ አምስት አመት የጠበቅኩ ሴት አንድ ቀን መታገስማ አያቅተኝም ከዚህ በኋላኮ ላርፍ ነው ተመስገን እያልኩ ብቻየን እስቃለሁ። ብዙ ሰዓታት አለፉ ስልኩ አይሰራም........ሲመጣ መንገድ ላይ የሆነ ነገር ገጥሞት እንደሆነ ደመደምኩ። ነፍሴ ተጨነቀች...... ሳላገኘው ምን ሆኖብኝ ይሆን? ብቻ ውስጤ ፈራ....... ግን መጠበቅ አላቆምኩም ።ካለፉት አምስት አመታት ጥበቃ ይልቅ የዛሬው ጥበቃ እንደ ሺ አመት ረዘመብኝ። ............
ጥበቃው ቀጠለ። አንድ መልዕክት ስልኬ ጋር እስኪገባ ድረስ። እንዲህ ይል ነበር......


" የኔ ማር አትጠብቂኝ ለዘላለም አልመጣም!!!!"

የዛ ሁሉ አመት ጥበቃ በአንድ አረፍተነገር አከተመ!!!! "አልመጣም" መልዕክቱን ደጋግሜ አየሁት ውስጤ ላይ የሆነ ነገር ቁርጥ ሲል ብቻ ተሰማኝ። አልጮህኩም፤ አላለቀስኩም። ምን እንደተሰማኝም አላውቅም ብቻ ግን ተሰበርኩ። ክንፏ እንደተመታ ወፍ ሙሽሽ አልኩ። ለካስ በጣም ሲታዘን እንባም ይደርቃል፣ ለመጮህም ቃላት ያልቃል።


ግን አንድ ነገር ልክ ነበርኩ። እንዳልኩት ዛሬ የመጨረሻ የጥበቃ ቀኔ ሆነ።ከዛሬ በኋላ አልጠብቅም!!!!




ከተቀመጥኩበት ተነስቼ በተሰበረ ልቤ ወደቤቴ መንገዴን ቀጠልኩ።

@nibab_lehiwot
@nibab_lehiwot
@nibab_lehiwot
በራሴ ውስጥ እየጠፋሁ እንዳለሁ ይሰማኛል። ከራስ ውስጥ ራስን ማጣት ልለው እችላለሁ። መሆን የምፈልጋት እኔን እየሆንኩ እንዳልሆነ ይታወቀኛል ግን ደግሞ የምፈልጋትን እኔን ለመሆን ምንም ጥረት አላደርግም። እንደምችል ይነግረኛል ግን............(ቃል አጠረኝ😥)በቃ



ከቀን ምሽትን ከ ፀሀይ ዝናብን የምመርጠው በምክኒያት ነው። በምሽት ማንም እንባየን አያይም ተፈጥሮ እንዳያይ ትከለክለዋለችና ለእኔ ግን የውስጤን ህመም ጨርሶ ባያድንልኝ እንኳን የታመቀውን ስቃይ ያስተነፍስልኛል። ማንም አየኝ አላየኝ አልሳቀቅም፣ ሰሙኝ አልሰሙኝ አልጨነቅም።በቃ ..........


በዝናብም እንዲሁ በጠብታው ከበሰበሰው አይኖቼ ውስጥ የሚወጣውን እንባ ማንም ሊያስተውለው አይችልም። በፈገግታ ውስጥ የተሸፈነ ትልቅ እንፋሎቴንን ከቀዝቃዛው የሰማይ ውሃ ጋር ተቀላቅሎ እንዲወርድ ያለማንም ከልካይ እፈቅድለታለሁ። ለትንሽ ሰዓታትም ቢሆን እፎይ እላለሁ።



አላውቅም ብዙ ሰወች እንደዚህ አይነት ህመም ውስጥ እንዳሉ ይሰማኛል። እንደሚቻል እያወቁ ማድረግ አለመቻል፣ ራስን መውቀስ፣ ዝቅ ማድረግ፣ ከራስ ጋ መጣላት፣ መታመም ከዛ በፈገግታ መሸፈን፣ ሰላምን መፈለግ፣ ርቆ መጥፋት መመኘት፣ ለምን የሚሉ ብዙ ጥያቄወች፣ መጠራጠር፣ ብዙ በጣም ብዙ ነገሮች ያመሳስሉናል።



ብቻ ግን ከዚህ ለመውጣት ይሄንን አድርጉ ብየ አልመክራችሁም እኔም እዛ ህመም ላይ ነኝና።
😔😔😔😔



@nibab_lehiwot
@nibab_lehiwot
የአለም ተፅእኖ ፈጣሪ ሰወች ምን ብለው ነበር????👇👇👇👇
ጥላቻን ወደ ኤሌክትሪክ መቀየር ቢቻል ኖሮ መላው አለምን ያበራል።

ኒኮላ ቴስላ
የተለየ ውጤት ከፈለግክ ተመሳሳይ ነገሮችን አታድርግ።

አልበርት አንስታይን
ማሰብ ከባድ ነው ለዚያም ነው ጥቂቶች የሚያደርጉት።

አልበርት አንስታይን
2025/05/12 23:41:37
Back to Top
HTML Embed Code: